1971
1971 አመተ ምኅረት
- መስከረም ፯ - የግብጽ ፕረዚዳንት አንዋር ሳዳት እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ሜናኽም ቤጊን በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር ሸምጋይነት፣ ከ፲፪ ቀናት የምሥጢር ድርድር በኋላ፤ በካምፕ ዴቪድ የካምፕ ዴቪድ ስምምነት ተፈራረሙ።
- መስከረም ፲፰ - በሮማ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር በፓፓነት የተመረጡት ቀዳማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ በተመረቁ በሰላሳ ሦስት ቀናቸው ሞቱ።
- ጥቅምት ፮ - ቫቲካን የተሰበሰቡ የዓለም ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳሳት፣ በ፬፻ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ጣሊያናዊ ያልሆኑትን በፖላንድ የክራካው ካርዲናል ካሮል ዮሴፍ ቮይትዋን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት (ፖፕ) በማድረግ መረጡአቸው። የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ቀዳማዊ ዮሐንስ ጳውሎስን በመተካት ፪፻፷፬ናው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነዋል።
- ጥቅምት ፲፯ - አንዋር ሳዳት እና ሜናኽም ቤጊን የዓመቱ የኖቤል የሠላም ሽልማት ተሸላሚዎች መሆናቸው ይፋ ሆነ።
- ታኅሣሥ ፩ - ሜናኽም ቤጊን እና አንዋር ሳዳት የኖቤል ሰላማዊ ሽልማት ተካፋዮች ሽልማቱን ተቀበሉ።
- መጋቢት ፲፯ - አንዋር ሳዳት እና ምናኽም ቤጊን በአሜሪካ ርዕሰ ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ የሰላም ውል ተፈራረሙ።
- ሚያዝያ ፫ - በታንዛኒያ መንግሥት ድጋፍ የተንቀሳቀሱ የኡጋንዳ ታጋዮች የአገሪቱን በትረ-ሥልጣን ከአምባ ገነኑ ኢዲ አሚን እጅ ፈልቅቀው ጨበጡ። አሚን ሸሽቶ ወደ ሊቢያ ኮበለለ።
- ሚያዝያ ፮ - ኢዲ አሚን ከተገለበጠ በኋላ ዩሱፍ ሉሌ የዩጋንዳ አዲስ ፕሬዚደንት በመኾን ቃለ መሀላቸውን ፈጸሙ።
- ሚያዝያ ፳፮ - በብሪታንያ ንጉዛት ማርጋሬት ታቸር የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ።
- ግንቦት ፳፬ - በቀድሞዋ ሮዴዚያ (አሁን ዚምባብዌ) በ፺ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ በጥቁሮች የሚመራ መንግሥት ሥልጣንን ጨበጠ።
- ሐምሌ ፱ - ሳዳም ሁሴን የኢራቅ ፕሬዚደንት ሆኑ።
- ጳጉሜ ፭ - ሆዜ ኤድዋርዶ ዶስ ሳንቶስ 2ኛው የአንጎላ ፕሬዝዳንት ሆኑ።
ክፍለ ዘመናት፦ | 19ኛ ምዕተ ዓመት - 20ኛ ምዕተ ዓመት - 21ኛ ምዕተ ዓመት |
አሥርታት፦ | 1940ዎቹ 1950ዎቹ 1960ዎቹ - 1970ዎቹ - 1980ዎቹ 1990ዎቹ 2000ዎቹ
|
ዓመታት፦ | 1968 1969 1970 - 1971 - 1972 1973 1974 |