Location via proxy:   [ UP ]  
[Report a bug]   [Manage cookies]                
Jump to content

ኤኳዶር

ከውክፔዲያ
(ከኢኩዋዶር የተዛወረ)

ኤኳዶር ሪፐብሊክ
República del Ecuador

የኤኳዶር ሰንደቅ ዓላማ የኤኳዶር አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Salve, Oh Patria

የኤኳዶርመገኛ
የኤኳዶርመገኛ
ዋና ከተማ ኪቶ
ብሔራዊ ቋንቋዎች እስፓንኛ
መንግሥት
{{{ፕሬዝዳንት
 
ራፋኤል ኮሬያ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
283,560 (73ኛ)
የሕዝብ ብዛት
የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት
 
16,144,000
ገንዘብ የአሜሪካ ዶላር
ሰዓት ክልል UTC −5 / −6
የስልክ መግቢያ 593
ከፍተኛ ደረጃ ዶሜን .ec


ኤኳዶር (Ecuador) በደቡብ አሜሪካ የሚገኝ አገር ሲሆን ዋና ከተማው ኪቶ ነው። በጐረቤቶቹ ኮሎምቢያፔሩ፣ እና በፓሲፊክ ውቅያኖስ ይዋሰናል። ይፋዊው ቋንቋ እስፓንኛ ነው። ኤኳዶር በእስፓንና «የምድር ወገብ» ማለት ሲሆን ስሙን ያገኘው በዚያው ኬክሮስ ላይ በመቀመጡ ነው።

የኤኳዶር ሪፐብሊክ ዴሞክራስያዊ ሀገር ሲሆን በፕሬዚደንት ይመራል። ከደቡብ አሜሪካ 1000 ኪ/ሜ. ወደ ምዕራብ በፓሲፊክ የሚገኙት ጋላፓጎስ ደሴቶች የኤኳዶር ናቸው። በተጨማሪ ኤኳዶር በተለያዩ ተፈጥሮአዊ መናኸሪያዎች በጣም ብዙ ልዩ ልዩ የዱር አራዊትና አትክልት አሉበት፤ ለምሳሌ የጋላፓጎስ ታላላቅ ባሕር ኤሊ። እነዚህ ኤሊዎች ከአንድ መቶ ዓመት በላይ በሕይወት ሊኖሩ ይችላሉ፣ አንዱ ኤሊ እንኳን የ170 ዓመታት ዕድሜ ነበረው። የተፈጥሮአዊ መናኸሪያ መብቶች በኤኳዶር 2000 ዓ.ም. ሕገ መንግሥት ተረጋግጠዋል።

ኤኳዶር ነፃነቱን በ1822 ዓ.ም. አገኘ። ከዚያ በፊት በስፓኒሽ መንግሥት ቅኝ ግዛት ለረጅም ጊዜ ስትሆን ለአጭር ጊዜ ደግሞ በግራን ኮሎምቢያ ሪፐብሊክ ውስጥ ተጨመረ። የነፃነቱ ትግል ለረጅም ዘመን ቆይቶ ብዙ የሰው ልጅ ሕይወት ፈጅቶ ነበር። ከዚያ ጀምሮ አገሩ ወይም ሲቪል ወይም ወታደራዊ መንግሥታት በመፈራረቅ ኖሮዋል። ምጣኔ ሀብቱ የተለማ ነው። የኗሪ ብሔሮችና አፍሪካዊ-ኤኳዶራውያን ሕዝብ ሁለቱም በኤኳዶር ባሕል ላይ ተጽእኖ በመሆናቸው የአስተዋጽኦ ሚና አጫውተዋል።