Location via proxy:   [ UP ]  
[Report a bug]   [Manage cookies]                
Jump to content

መግነጢስ መስክ

ከውክፔዲያ
የመግነጢስ መስክን አቀማመጥ በሚያሳይ መልኩ የብረት ቁርጥራጮች በመግነጢሱ ዙሪያ የሚሰሩት ትዕይንት። መስከመሮቹ የተጠጋጉ ከሆኑ መግነጢሱ ሃይለኛ ነው እንላለን፣ ከተራራቁ ደግሞ ደካማ ነው እንላለን።
Hans Christian Ørsted, Der Geist in der Natur, 1854

መግነጢስ መስክ ማለቱ አንድ መግነጢስ ጉልበት የሚያሳርፍበት ከባቢ ዙሪያ ነው። መስኩ ከጉልበት መስክ የተሰራ ሲሆን አፈጣጠሩም በሚንቀሳቀሱ የኤሌክትሪክ ሙላቶች፣ ከጊዜ አንጻር በሚለዋወጥ የኤሌክትሪክ መስክ እና በራሳቸው በአተም እኑሶች የተፈጥሮ መግነጢሳዊ ባህርይ ናቸው። የመግነጢስ መስክ በአንድ ነጥብ ላይ ባለው ጥንካሬ እና አቅጣጫ ይወሰናል፣ ስለሆነም የቬክተር መስክ አይነት ነው ። መግነጢሳዊ መስክ ብዙ ጊዜ የሚተረጎመ በተንቀሳቃሽ የኤሌክትሪክ ሙላቶች ላይ በሚያሳርፈው ሎሬንዛዊ ጉልበት ነው።

መግነጢሳዊ መስክ ከጥንት ጀምሮ ለሰው ልጆች ጠቀሜታን አበርክቷል። ለምሳሌ ሰዎች ምድር ስለምታፈልቀው መግንጢሳዊ መስክ መገንዘባቸው ኮምፓስ ሰርተው አለምን ማሰስ እንዲሁም የሚገኙበትን አንፃራዊ ቦታ እንዲያውቁ አስችሏል። በአሁኑ ዘመን ተሽከርካሪ የመግነጢስ መስኮች ኤሌክትሪክ ለማመንጨትና የኤሌክትሪክ ሞተሮችን ለማንቀሳቀስ በመርዳት የዘመናዊ ህይወት መሰረት ሆነዋል።