Location via proxy:   [ UP ]  
[Report a bug]   [Manage cookies]                
Jump to content

ጋሜር

ከውክፔዲያ

ጋሜር (ዕብራይስጥגֹּמֶר /ጎሜር/) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 መሠረት የያፌት በኲር ልጅና የአስከናዝ፣ የሪፋትና የቴርጋማ አባት ነበር። በመጽሐፈ ኩፋሌ ደግሞ ስሙ «ጎሜር» (ወይም አንዴ በግድፈት «ሰሜር») ሆኖ ይታያል።

አይሁድ ታሪክ ጸፈፊ ዮሴፉስ (1ኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም.) እንዳለው፣ «ጎሜር ግሪኮች አሁን 'ገላትያውያን' የሚሏቸውን፣ በድሮ ግን 'ጎመራውያን' የተባሉትን ሰዎች የመሠረተ ነበር።»[1] በእርግጥ የገላትያ ስም የመጣ በዚያ አገር ከሰፈሩት ጋሊያውያን (ኬልቶች) ነበረ። ዳሩ ግን አቡሊድስ የተባለው ክርስቲያን ሊቅ (226 ዓ.ም. ግድም) ጎሜር የቀጴዶቅያውያን አባት እንደ ሆነ ጽፏል።[2] ሄሮኒሙስ (380 ዓ.ም. ግድም) እና ኢሲዶር ዘሰቪል (590 ዓ.ም. ግድም) ግን የዮሴፉስን ቃል ተከትለው የጎሜርን መታወቂያ ከገላትያን፣ ጋሊያውያንና ኬልቶች ጋራ አንድላይ አደረጉ።

በአሁኑ ዩክራይን በጥንት የኖረው ኪመራውያን (ወይም ጊመራውያን፣ ሲሜራውያን) ሕዝብ ከ700 ዓክልበ. በኋላ ወደ እስያ ወርረው ከአሦር መንግስት ጋራ ተጣሉ። እነዚህ የጎሜር ዘሮች እንደ ተቆጠሩ በሰፊ ይታስባል፤ ለምሳሌ በአማርኛው «መጽሐፍ ቅዱስ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከማጥኛ ጽሑፍ ጋራ» ስለ ጋሜር እንዲህ ይላል፦ «የጋሜር ሕዝቦችና ነገዶች በጥቁር ባሕር አካባቢ ይኖሩ ነበር (በኋላ ሲሜራውያን ወይም ጋሜራውያን ተብለዋል)።»

ከዚህ በላይ በ200 ዓክልበ. ግድም በአሁኑ ዴንማርክ የኖረ ኪምብሪ ሕዝብ ከዩክራይኑ ኪሜራውያን ጋር አንድላይ እንደነበሩ ከጥንት ጀምሮ ተብሏል። ይህ ኪምብሪ ሕዝብ መጀመርያ ከኬልቶች ወገኖች ጋር ተቆጠረ፣ በኋላም ከጀርመናውያን ወገኖች መካከል ተገኙ። በ1578 ዓ.ም. የእንግሊዝ ታሪክ ጸሐፊ ዊሊያም ካምደን ባሳተመው መጽሐፍ ዘንድ፣ እነዚህ ኪምብሪ እና ኪመራውያን የጎሜርን ስም ሲጠብቁ፣ የኬልቶችም አባቶች ሲሆኑ፣ ይህን የሚያመልከት እስከ ዛሬ ድረስ የዌልስ ኗሪዎች በራሳቸው ቋንቋ «ኪውምሪ» መባላቸው ነው አለ።[3].

ከካምደን በኋላ ብዙዎቹ ጸሐፍት ከ17ኛው እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመናት ድረስ ይህን አሳብ ተቀበሉ። የዛሬው ዌልሽኛ ሊቃውንት ግን ይህን አያምኑም። በ1845 ዓ.ም. ዮሐን ካስፓር ዞይስ እንደ ገመተው፣ ይህ ሳይሆን «ኪውምሪ» የሚለው ስም የመጣ ከብሪታንኛ ቃል *«ኮምብሮገስ» (ማለት 'ባላገር') ይሆናል ባዮች ናቸው።[4][5]

በአይሁዶች ተልሙድ ዘንድ፣ ጎሜር የ«ጎሜርማውያን» (ጀርመናውያን) አባት ነበር።

እስላም ጸሓፊው አል ታባሪ (905 ዓ.ም. ግድም) ስለ ጎሜር ዕድሜው እስከ ሺህ አመት ድረስ እንደ ደረሰ የሚል የፋርስ ልማድ ተረከ።[6]

1490 ዓ.ም. አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ የተባለ ጣልያናዊ መነኮሴ ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ የባቢሎን ታሪክ ጸሓፊ ቤሮሶስ (290 ዓክልበ.) ስለ ኖኅ ልጆች ብዙ መዝገቦች አቅርቦ ነበር። በዚህ በኩል፣ በናምሩድ 10ኛው ዓመት የያፌት ልጅ «ኮሜሩስ ጋሉስ» (ጋሜር) የሰፈረበት አሁን ጣልያን የተባለው ሀገር ሆነ። ከ30 ዓመት በኋላ ግን ሌሎች ከዚህ ኮሜሩስ ዘር በባክትሪያ እስከ ጋንጅስ ወንዝ ድረስ ሠፈሩ። ከዚህም እንደገና 20 አመት በኋላ፣ ኮሜሩስ የሠረገላና የጋሪ ዕውቅት ከእስኩቴስ ተመልሶ ወደ ጣልያን አስገባ። ከዚያም 8 ዓመት በኋላ ልጁ ኦኩስ ወዩስ እንደ ተከተለው ይባላል። በተጨማሪ የሳርማትያና የጀርመን መስራች ቱዊስኮን ሲሆን፣ በአንዳንድ ጸሄፊ ዘንድ የሱ መታወቂያና የጋሜር ልጅ አስከናዝ አንድላይ ነው። ዘሬ ግን አብዛኛው መምህሮች የአኒዩስን ጽሑፍ እንደ ሐሣዊ መረጃ ይቆጥሩታል።

በደቡብ ቻይናና ጎረቤቱ የሚኖረው ምያው ብሔር ልማዳዊ ታሪክ ዘንድ፣ ከጋሜር («ጎመን») እና ከሚስቱ ጎዮንግ ተወለዱ።[7]

የጋሜር ልጆች የወለዷቸው ወገኖች መታወቂያ በተለያዩ ምንጮች ዘንድ እንዲህ ነው፦

ደግሞ ይዩ፦ ሁኖርና ማጎር
  1. ^ ፍላቪዩስ ዮሴፉስ፣ የአይሁዶች ጥንታዊነቶች, I:6.
  2. ^ Chronica, 57.
  3. ^ Camden's Britannia, I.17,19.
  4. ^ Lloyd, p. 192
  5. ^ University of Wales Dictionary, vol. I, page 770.
  6. ^ Tabari, Prophets and Patriarchs (Vol. 2 of History of the Prophets and Kings)
  7. ^ ዘፍጥረት በምያው ሕዝብ ዘንድ(እንግሊዝኛ)