Location via proxy:   [ UP ]  
[Report a bug]   [Manage cookies]                
Jump to content

ፈቃድ

ከውክፔዲያ

ፈቃድ ማለት ከአንድ ሰው ውስጣዊ ግፊት የሚመነጭ ድርጊት ነው። ውስጣዊ ግፊት ማለት ግለሰቡ በራሱ አዕምሮ ሙሉ ቁጥጥር የጠነሰሰው ማለት ነው። ለምሳሌ አበበ ሳያስበው ድንገት መኪና ቢገጨው ይህ ድርጊት የአበበ ፈቃድ ነው አይባልም። ሆኖም ግን አበበ ስራየ ብሎ በመኪና ቢገጭ፣ ያ እንግዲህ የአበበ ፈቃድ ነው ይባላል።

ፈቃድ የፍላጎት አይነት ሲሆን ልዩነታቸው ፈቃድ ሙሉ በሙሉ በአንድ ግለሰብ አዕምሮ የሚጠነሰስና በድርጊትም የሚገለጽ ሲሆን፣ ፍላጎት አልፎ አልፎ በውጭ ተፅዕኖ የሚፈጠር መሆኑና የግዴት በድርጊት አለመገለጹ ነው።