Location via proxy:   [ UP ]  
[Report a bug]   [Manage cookies]                
Jump to content

ሂና

ከውክፔዲያ
?ሂና
ሂና
ሂና
ሳይንሳዊ ደረጃ መስጫ
ስፍን: አትክልት (Plantae)
ክፍለመደብ: የባርሰነት ክፍለመደብ Myrtales
አስተኔ: የሂና አስተኔ Lythraceae
ወገን: የሂና ወገን Lawsonia
ዝርያ: ሂና (L. inermis)

ሂና Lawsonia inermis (ወይም እንሶስላ) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

የአንዳንድ አገር ሴቶች በዚህ ተክል ለቆዳቸው ምልክት ለማድረግ ቀለም ይሠራሉ።

«እንሶስላ» ባብዛኛው ለሌላ ዝርያ (Impatiens tinctoria) ያጠቁማል።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በወገኑ (Lawsonia) ውስጥ አንድያው ዝርያ ነው። ከዚያ በላይ የሂና አስተኔ (Lythraceae) ሩማን አለበት።

ሂና ረጅም ቊጥቋጦ ወይም ትንሽ ዛፍ ሊባል ይችላል፤ ከ1.8 እስከ 7.6 ሜትር ሊደርስ ይችላል። መላጣ፣ ብዙ ቅርንጫፍ ያለ፣ ትንንሽም ቅርንጫፎች እንደ እሾሕ ናቸው።

ቅጠሎቹ በአገዳው ላይ ፊት ለፊት ይበቅላሉ፤ ቅጠሉም ዘንጋልባ፣ ሞልሟላ፣ የሥላጢን ቅርጽ ያላው (ረጅምና በመሃሉ ሰፊ)፣ የሾለ፣ እና በዘበናይ ገጽታ ረባዳ ስርወት አለው።

የሂና አበባ አራት አበባቃፎች በ2 mm ቱቦ እና የተዘርጋ ግርብ 3mm አሉት። ያበባውም ቅጠል ሞላላ ነው፣ ነጭ ወይም ቀይ ወንዳካሎች በአበባቃፎች ቱቦ ጫፍ ላይ በጥንዶች ይገኛሉ። እንቁልጢው ባለ አራት ህዋስ፣ በ5 mm ዘለግ ይላል።

የሂና ፍሬ ትንንሽ ቡናማ ቀለህሞች፣ 4-8 mm ባጋማሽ፣ 32-49 ዘሮች በየፍሬው፣ በአራት ኢመደበኛ ስንጥቆች ይከፈታል።[1]

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የሂና ተክል ለስሜን አፍሪካ፣ ምዕራብና ደቡብ እስያ፣ እና ስሜን አውስትራልስያ በገሞጂና በከፊል ድርቅ በሆኑ ዙርያዎች ኗሪ ነው።[2]

ከ35 እስከ 45 ዲግሪ ሴንቲግሬድ መካከል ሙቀት ሲታደግ የበለጠውን ቀለም ያስገኛል።[3]

የዝናብ ወራት ከጀመረ በኋላ በቶሎ አዲስ ቡቃያ ያበቅላል። ከዚያ እድገቱ ዝግ ይላል። ቅጠሎች ቀስ በቀስ ቢጫ ሆነው በደረቅ ወይም ቅዝቃዛ ሰዓት ይወድቃሉ። ሙቀቱ ከ11 ዲግሪ በታች ከሆነ አይዳብርም፤ ከ5 ዲግሪ በታች ቢሆን ተክሉን ይገድላል።

የተክሉ ጥቅም

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
  • መኖ - ቅጠሎቹ በከብት ይበላሉ።
  • ማገዶ - እንጨቱ ይመቻል።
  • እንጨቱ ረቂቅ-ኢኒን፣ ጽኑ ሲሆን በሕንድ አገር ለድንኳን ችካል፣ ለመሳርያ መያዣ ይጠቀማል። በኢንዶኔዥያም ትንንሹ ጭራሮች ልጥርስ መፋቂያ፣ አበቦችም ለሽቶ ይጠቀማሉ።
  • ጭረት - በቱርካና ኬንያ አገዳው ለአሣ አጥማጅ ቅርጫት ይጠቀማል።
  • ቀለም - በተለይ በእስላም አገራት፤ ቅጠሎችና ትንንሽ ቡቃያዎች በማድቀቅ፣ ቡላ-አረንጓዴ ዱቄት ይሠራል። ዱቄቱም በሻይሎሚ ጭማቂ በማራስ ብርቱካን-ቀይ ቀለም ይሠራል። ቆዳ፣ ጸጉር፣ ጨርቅ፣ እንጨት ለማጌጥ ይችላል።
  • ባህላዊ መድኃኒት - ሥሮቹ ለጨብጡ መድኃኒት እንዲሁም ለሴቶች ወላድነት ለመጨምር ይቆጠራሉ። የሥሮቹ መረቅ ለሽንት መድኃኒት ወይም ለደረት ጉሮሮ ቁስል እንደ ጠቃሚ ይቆጠራል።

ቅጠሉ የጸረ-ባክቴሪያ ጸባይ lawsone እንዳለው ይታስባል። የቅጠልና የአበባ ጭማቂ ለቆላ ቁስልና ለቁርጥማት በአፍአ፣ ወይም ለመንጋጋ ቆልፍ፣ ለሚጥል በሽታ፣ ለሆድ ቁርጠትም በአፍ ይሰጣል። እንዲሁም ቅጠሉ ለቁምጥና፣ ለወፍ በሽታ፣ ወይም ለእስከርቪ ይሰጣል።

ቁርጥ አርገው የሚስቡ ሥሮቹ ተደቅቀው፣ በልጆች ብጉንጅና የዓይን በሽታ ለማከም በራስ ላይ ይቀባል።

ማሌዥያ፣ በእግሮች የመቃጠል ስሜት ለማስታገሥ የተቀጠቀጠ ትኩስ ቅጠል ይጠቀማል፣ እንዲሁም ለቤሪቤሪ፣ ለቆዳ በሽታ፣ ለብጉንጅ፣ ለግዝረት ቁስል፣ ለሆድ እባጭ፣ ይጠቀማል። ለድድ ብጉንጅ መረቁ ተጉመጠመጠ፣ ወይም በመውለድ ለሆድ ህመም ይሰጣል።

በኢንዶኔዥያ፣ የቅጠሎች ለጥፍ ለጥፍር በሽታ እና ለችፌ ልክፈት ይሰጣል፤ የቅጠሎች ሻይ ውፍረት በሽታ እንደሚከለክል ይባላል፤ ከታናናሽ ፍሬዎችም የተሠራ ቅባት ለእከክ ያከማል።

ፊሊፒንስ አበቦቹ የሚጫጫን ወይም ለእንቅልፍ እንደሚረዱ ይነገራል።[4]

  1. ^ Kumar S., Singh Y. V., & Singh, M. (2005). "Agro-History, Uses, Ecology and Distribution of Henna (Lawsonia inermis L. syn. Alba Lam)". Henna: Cultivation, Improvement, and Trade. Jodhpur: Central Arid Zone Research Institute. pp. 11–12. OCLC 124036118. 
  2. ^ "henna (plant)". Encyclopædia Britannica. Retrieved 5 May 2013. 
  3. ^ Bechtold, Thomas; Mussak, Rita (6 April 2009). Handbook of Natural Colorants. John Wiley & Sons. p. 155. ISBN 9780470744963. 
  4. ^ Orwa C, A Mutua, Kindt R , Jamnadass R, S Anthony. 2009 Agroforestree Database:a tree reference and selection guide version 4.0 መረጃ ስለ ሂና በእንግሊዝኛ