Location via proxy:   [ UP ]  
[Report a bug]   [Manage cookies]                
Jump to content

ጉዴአ

ከውክፔዲያ
የጉዴአ ምስል።

ጉዴአ ከ2009 እስከ 1989 ዓክልበ. ግድም የላጋሽ ከተማ ገዢ (ኤንሲ) በሱመር ነበር። ኡርባባን ተከተለው፣ ይህ ከአካድ መንግሥት ውድቀት በኋላ ሲሆን ላጋሽና ሌሎች የሱመር ከተሞች በተግባር ነጻነታችውን ከአካድ አገኝተው ነበር። ጉዴአ የኡር-ባባን ሴት ልጅ ኒናላን አገባትና ኤንሲ-ነቱን እንዲህ ወረሰ።

ከነገሡት ፳ ዓመታት ለሁላቸው «የዓመት ስም» ይታወቃል። ስለዚህ ፮ኛው ዓመቱ (2004 ዓክልበ. ግድም) «አንሻን በመሣሪያዎች የተመታበት ዓመት» በመባሉ ወደ ኤላም መዘመቱ ይዘገባል።[1] አንሻንና ኤላም በዚያን ጊዜ በንጉስ ኩቲክ-ኢንሹሺናክ ሥር እንደ ነበሩ ይመስላል።

በተረፈ በጉዴአ ዘመነ መንግሥት ብዙ ሕንጻዎች እንደ ቤተ መቅደሶች በየከተማ ይገነቡ ነበር። ላጋሽ ከብዙ አገራት ጋር ንግድ ስላካሄደ፣ ሀብታም አገር ሆነ። የጉዴአን መልክ የሚያሳዩ ፳፮ ሐውልቶች ተገኝተዋል።

ጉዴአ በልጁ 2 ኡር-ኒንጊርሱ ተከተለ። ከጉዴአ በኋላ በላጋሽ የገዙት ኤንሲዎች ሁሉ ድካሞች ነበሩና በቅርብ ጊዜ ውስጥ የዑር ንጉሥ ኡር-ናሙ አዲስ ሱመራዊ መንግሥት አገሩን ያዘ።

ቀዳሚው
ኡር-ባባ
ላጋሽ ኤንሲ
2009-1989 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
2 ኡር-ኒንጊርሱ
  1. ^ የጉዴአ ዓመት ስሞች