Location via proxy:   [ UP ]  
[Report a bug]   [Manage cookies]                
Jump to content

ፕላቶ

ከውክፔዲያ
የፕላቶ ምስል

ፕላቶ በጣም ዋና የጥንት ግሪክ ፈላስፋ ነበር፣ የኖረበትም ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት 427ዓ.ዓ. እስከ 348 ዓ.ዓ. ነበር። የሶቅራጠስ ተማሪና የአሪስጣጣሊስ አስተማሪ ነበር። ፕላቶ ብዙ የፍልስፍና ሃሳቦችን በመጻፍ ይታወቃል። እንዲያውም አልፍሬድ ዋይትሄድ የተሰኘው ዘመናዊ የእንግሊዝ ፈላስፋ ሲናገር "ከፕላቶ በኋላ የተጻፉ ፍልስፍናወች በሙሉ በፕላቶ ስራ ላይ የተነሱ አስተያየቶች" ናቸው በማለት የፕላቶን የሃሳብ ስፋትና ጥልቀት አስምሮበታል።

የፕላቶ መጽሐፎች የሁለት ሰው ውይይት ቅርጽ ነበራቸው። ሰወች እርስ በርስ ስለ ሃሳቦች እያወሩ፣ አልፎ አልፎም እየተቃወሙ፣ በሚያሳይ ሁኔታ ይቀርቡ ነበር። ስለሆነም የፕላቶን መጻህፍት ለማንበብ ደስ ይላሉ።

አብዛኛው የፕላቶ መጽሐፍ ዋና ተናጋሪ ሶቅራጠስ ሲሆን፣ ይህ ተዋናይ ሌሎችን ሰወች ሲጠይቅ፣ ከሚያምኑት ነገር አምክንዮ የሌለውን ክፍል ለማግኘት ሲሞክርና ሰዎቹ በተራቸው በዚህ ምክንያት ሲበሳጩ ያስነብባል። ያሁን ዘመን ተመራማሪወች የፕላቶው ሶቅራጠስ ንግግሮች እውነት የሶቅራጠስ ንግግሮች ይሁን ወይንም ፕላቶ የፈጠረው ገጸ ባህርይ፣ ለመወሰን አዳጋች መሆኑን ይገልጻሉ።

ከፕላቶ መጻሕፍት ውስት ሪፐብሊክ የተሰኘው በዋናነት ተጠቃሽ ነው። በዚህ ስራው ሶቅራጠስ ለሰው ልጅ የተስተካከለ አገር ብሎ ያሰበውን ምናባዊ አለም ገልጿል። በዚያውም ታዋቂውን የሶቅራጠስ ዘዴ ተብሎ የሚታወቀን የምርምር ስልት አስተዋውቋል። ከዚህ በተረፈ [[የፕላቶ ህግ|ህጎች| የተሰኘውን መጽሃፍ ይሄው ፈላስፋ ደርሷል።

ዋቢ መጻህፍት

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የ ፕላቶ አሰተዋዖኦ

Lavine, T.Z. (August 1989). From Socrates to Sartre: the Philosophic Quest. Bantam Books. ISBN 0-553-25161-9.